ለአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት በሙሉ

አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት መስከረም 12 ቀን 2015 ዓ/ም በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል(በቀድሞው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል) ከጠዋቱ 2፡3ዐ ጀምሮ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምከር ቤት ፕሬዚዳንት፣ ም/ፕሬዚዳንትና የቦርድ አባላት ምርጫም ይካሄዳል፡፡ ይህ ምርጫ ግልጽና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ከፍተኛ ልምድና የሥራ ፍላጐት ያላቸው አባላት የሚገኙበት የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቋቁሟል፡፡
ኮሚቴው ለፕሬዚዳንትነት፣
ለም/ፕሬዚዳንትነትና ለዲሬክተሮች ቦርድ አባልነት ቦታዎች የሚጠቆሙትን ዕጩዎች ይቀበላል፡፡ ስለሆነም የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት አባላት ለዕጩዎች በወጣው መስፈርት መሠረት ለተጠቀሱት ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ራሳችሁንም ሆነ ብቃት ያላቸውን ሌሎች አባላት እንድትጠቁሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ለጥቆማውም ከዚህ መልእክት ጋር አባሪ በሆነው ሰነድ፤ ወይም ከምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ቢሮ፤ ወይም ከምክር ቤቱ ድረገጽ ላይ ( www.addischamber.com ) የመስፈርቱን ዝርዝር እና የዕጩዎች መጠቆሚያ ቅጽ ከሞላችሁ በኋላ የተሞላውን ቅጽ በኤንቨሎፕ አሽጋችሁ አድራሻውን ለምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚል እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰዐት ድረስ በአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ቢሮ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጥቆማ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *