በንግድ ምዝገባ፤ፈቃድ እና ቁጥጥር ረቂቅ መመሪያ ላይ የባለድርሻዎች ውይይት ተካሄደ

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሐሰን መሐመድ እንዳሉት መመሪያው የንግድ ሥርዓቱን በማሻሻል ሀገራችንን ለንግድ ሥራ የተሻለች ምቹ ለማድረግ ይረዳል ፡፡
መመሪያው በወረቀት ሥራዎች እና ምልልስ አሰራርን በመቀየር የንግድ ምዘገባ ፤ፈቃድ እና ዕድሳት ከለበት ቦታ ሆኖ በኦንላይን አገልግሎት መጠቀም ያስችላል ብለዋል፡፡

የኢትየጵያ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዚዳንት መላኩ እዘዘው በበኩላቸው መንግሥት አሁን የጀመረው ኦንላይን አገልግሎት ተጠያቂነት እና ግልጽ አሰራርን የሚያበረታታ ነው፡፡
ምክር ቤታቸውም የንግዱን ህብረተሰብ በማሳተፍ ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓት ለማምጣት በትብብር ለመሠራት ዝግጁ መሆኑን አመልክተዋል ፡፡

ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አቶ ዮሐንስ ወ/ገብርኤል በሰጡት አስተያየት መመሪያው የተሻለ የንግድ ከባቢ ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው መመሪያው በወረዳዎች አካባቢ ያሉ ወጥነት የሌለው አሰራሮችን እንዲፈትሽ ጠይቀዋል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ሚ/ር ለግብዓት ማሰባሰቢያ ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ 10 ክፍሎች እና 65 አንቀጾች አሉት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *