በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ በናይሮቢ የልምድ ልውውጥ ስልጠና እየተካፈለ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የልዑክ ቡድን አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል።

በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ በናይሮቢ የልምድ ልውውጥ ስልጠና እየተካፈለ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት የልዑክ ቡድን አባላት ጋር በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ውይይት አካሂደዋል። በውይይቱም ወቅት ክቡር አምባሳደር ባጫ ሚሲዮኑ በኢኮኖሚና ቢዝናስ ዲፕሎማሲ ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ይቻል ዘንድ እንደአዲስ አባባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ካሉ የአገራችን ተቋማት ጋር በቅንጅት እና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በኬንያ የሚገኙ ታዋቂ ባለሀብቶች ወደ አገራችን ገብተው መዋዕለ-ነዋያቸውን እንዲያፈሱ እና የአገራችን የወጪ ምርቶችን በኬንያ ገባያ የተሻለ ተቀባይነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የልምድ ልውውጡ የሚኖረውን አስተዋጽኦ የጠቀሱት አምባሳደሩ፣ የንግድ ማህበሩ እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲሳካ ሚሲዮኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠውላቸዋል።

የአዲስ አበባ ንግድንና ዘርፍ ማህበራት የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን በበኩላቸው በኤምባሲው ለተደረገላቸው ድጋፍና ለቀረበላቸው ገለጻ አመስግናው በቀጣይ ሀገራችን ከኬንያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ሚሰሩ ስራዎች የንግድ ማህበሩ ተገቢ መረጃዎችን በመለዋወጥና ከሚሲዮኑ ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

የልኡካን ቡድኑ ከነሃሴ 17- 20 ቀን 2014 ዓ.ም በኬንያ በሚኖረው ቆይታ እያደረገ ከሚገኘው የልምድ ልውውጥና ስልጠና ጎን ለጎን በኬንያ የሚገኙ ታዋቂ የንግድ ማህበራትን እና ባለሃብቶችን አግኝተው ውይይት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *