በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን በዘላቂ ሁኔታ ለመርዳት አዲስ ቻምበር ቁርጠኝነቱን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ( አዲስ ቻምበር) በሀገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ እየሰፋ የመጣውን ድህነት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችና የዋጋ መናር በዜጎች ላይ እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመገንዘብ የማህበራዊ ሃላፊነት ተግባሩን ለመወጣት የሚያስችለውን ድጋፍ ዛሬም ቀጥላል፡፡

ምክር ቤቱ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ 185 ዜጎች የዘይት፤ ፓስታና ሩዝ እንዲያገኙ አድርጋል፡፡

የንግድ ምክር ቤቱ ፕረዚደንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤ የምግብ እርዳታውን ባስረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር እርዳታ ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል የተናገሩ ሲሆን ምክር ቤቱ ዜጎች በስራ ፈጠራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ እንደሚያመቻች ተናግረዋል፡፡

አቶ ሰይድ ሻፊ የወረዳ አምስት ዋና ስራ አስፈጻሚ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር ንግድ ምክር ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ በማመስገን ዜጎች ከእርዳታ ባለፈ ኑራቸውን ዘላቂነት ባለው መልኩ የሚመሩበት መንገድ እንዲመቻች ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ይህን ለማሳካት የግሉ ዘርፍ አይነተኛ ሚና መጫወት እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

የግሉ ዘርፍ ጥምረት በኑሮ ውድነት ላይ ትኩረቱን ባደረገው ፕሮጀክት ከባለፉት ሶስት ወራት ጀምሮ በርከታ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *