አምስተኛዉ የአዲስ ቻምበር አለም አቀፍ ልዩ የማኑፋክቸሪንግ እና የቴክኖሎጂ የንግድ ትርዒት ተከፈተ፡፡

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢንደስትሪ ሚኒስትሩን አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች  እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትም ተገኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ሃጋራችን ያሏትን አወንታዊ ተመራጭነት ጠቅሰዉ በአምራቾች ተፈላጊነቷ ከፍ እያለ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡
የጥሬ እቃ እና የገበያ ችግሮችን ለመፍታት በማክሮ ደረጃ ማሻሻያዎች እየተጠኑ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የግሉን ዘርፍ ጤናማ ፉክክር እናበረታታለን ያሉት ሚኒንትሩ፣ አምራቾችን በ”ኢትዮጲያ ታምርት” ንቅናቄ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ድጋፍ ሲደረግላቸዉ መቆየቱን እንዲሁም ድጋፉም ለቀጣዩ 10 አመታት እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
ሚኒስትሩ የሃገር ዉስጥ አምራቾች እና የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች መንግስት ምቹ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ቁርጠኛ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ኤክስፖዉ ከመሸጫ በላይ የንግድ ትስስር የሚፈጠርበት እንደሚሆን ተስፋቸዉን አጋርተዋል፡፡
የቻምበሩ ፕሬዝደንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ ቴክኖሎጂን የሚያበረታታ የንግድ ትርዒት እንደሚሆን የጠቆሙ ሲሆን፣ የ10 አመቱ የመንግስት እቅድ የግሉን ዘርፍ የማበረታታት መሆኑን በማስታወስ አምራቹን የበለጠ የሚደግፍ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የዉጭ ድርጅቶችንም በኤግዚቢሽኑ በመሳተፍ ከኢትዮጲያ አምራቾች እና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል፡፡

ቴክኖሎጂ ቅንጦት አይደለም ያሉት ፕሬዝደንቷ፤ ዘርፉን በማስፋፋት የውጭ ምርቶችን መተካት የስራ አጥነትን መቀነስ እና ተመሳሳይ የኢኮኖሚ ሴክተሮችን ማጎልበት ይገባል ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *