አዲስ ቻምበር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለአንድ መቶ ችግረኞች 135ሺ ብር የሚያወጣ የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ፡፡

ንግድ ምክር ቤቱ ያደረገው ድጋፍ ከክፍለ ከተማው 14 ወረዳዎች ለተውጣጡ 100 ችግረኛ ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 5 ሊትር ዘይትና ፣ 5 ኪ.ግ ዱቄት ነው ፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሽንቁጤ ድጋፉ የመጀመሪያ አለመሆኑን አውስተው ፤ የአሁኑ ድጋፍ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተደረገ ነው ብለዋል ፡፡

ድጋፉ ዛሬ ለይ ያለባችሁን ችግር መቅረፍ እንጅ ሁሌም ተረጅ ማድረግ አይደለም ያሉት ወ/ሮ መሰንበት ነገ ከችግራችሁ ወጥታቸሁ ጠንክራችሁ እንድትሰሩ ማለም ነው ብለዋል::

የቦሌ ክ/ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መሰፍን ኃይሌ ድጋፉ ያለባችሁን ችግር ሙሉ በሙሉ ይቀርፋል ማለት ሳይሆን መተሳሰብን ለማሳየት ነው ብለዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *