የሀዘን መግለጫ

 

1944-2012 ዓ፣ም
በአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በምክትል ዋና ፀሃፊነት እና በልዩ አማካሪነት ያገለገሉት አቶ ተፈሪ አስፋው ከዚህ አለም በሞት መለየት ምክር ቤታችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ ለባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡
አቶ ተፈሪ አስፋው ከ1992 ዓ፣ም ጀምሮ በምክር ቤቱ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን እየገለጽን በምክር ቤቱ የተዉት አሻራም ለወደፊቱ በታሪክ የሚታወስ ይሆናል፡፡
የምክር ቤታችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ማኔጅመንትና መላው የምክር ቤቱ ሰራተኞች በአንጋፋው ባልደረባችን ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በግሉ ዘርፍ ስም እየገለጽን ለንግዱ ህብረተሰብም ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ክብር የሚሰጠው ነው፡፡
አዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት