የክሬዲት ዋስትና አስፈላጊው የህግ ማእቀፍ ተዘጋጅቶለት እንዲተገበር ተጠየቀ

የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት የክሬዲት ዋስትና ( credit insurance guarantee for promoting trade ) አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሒዷል።
የ ኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ያሬድ ሞላ የውይይትመነሻ ሀሳብ ያቀረቡ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሠጥተዋል። አቶ ያሬድ እንደገለፁት የክሬዲት ዋስትና አለማችን ከ18ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገችው ስርአት ነው።
በኢትዮጵያ ግን የክሬዲት ዋስትና መስጠት የሚያስችል ህግ የለም ብለዋል። ይህ የዋስትና አይነት ለግሉ ዘርፍ መስፋፋት ብሎም ለሀገር እድገት አስፈላጊ በመሆኑ ነጋዴውን ሊጠቅም በሚችል እና በተጠና ሁኔታ ሊተገበር እንደሚገባ አቶ ያሬድ ገልጸዋል ።
በዚህ ረገድ በማንኛውም ሰአት አገልግሎቱን ለመጀመር በኢንሹራንስ ኩባንያዎች በኩል ዝግጁነት እንዳለ የገለፁት አቶ ያሬድ ነገር ግን የብሔራዊ ባንክ ይሁንታ እና የሚያሰራ የህግ ማእቀፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ።