25ኛው የአዲስ ቻምበር አለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ተከፈተ

የወጪ ንግድ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው አለም አቀፍ ንግድ ትርዒት ከ 70 በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች ተሳትፈውበታል፡፡

በእለቱ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ እንዳለው መኮንን::

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት፡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ባለድርሻዎች ተገኝተዋል፡፡

ንግድ ትርዒቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩትን በአንድ የሚያገናኝ መሆኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ እንዳለው መኮንን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የገለፁ ሲሆን የወጭ ንግድን ለማሳደግ የሃገር ውስጥ አምራቾችን ማበረታታት እና ማገዝ ቀዳሚ ስራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

አክለውም ንግድ እና ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት መንግስት መሰረተ ልማትን በማመቻችት እና የፖሊሲ እንዲሁም መመርያዎችን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ የሚያምንበት መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ለዚህም የአዲስ አበባ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የፖሊሲ ግብአቶችን በማቅረብ አጋር እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጤም በበኩላቸው የወጭ ንግድ መጠን ዝቅተኛ መሆን የኢኮኖሚ እድገትን ወደኋላ የሚጎትት መሆኑን ገልፀው የወጭ ንግድን ለማሳደግ መሰረታዊ የሆኑ ማሻሻያዎችን መውሰድ እና መተግበር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የንግድ ስራ በቀደመው መንገድ ብቻ የሚከናወን ውድድሩም ከተለመዱት ጋር ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቷ ይህንን ከግምት በማስገባት ፖሊሲ አውጭዎችም ሆኑ የንግድ አንቀሳቃሾች ትኩረታቸው ሊሆን የሚገባው የሃገር ውሰጥ የንግድ አንቀሳቃሾች ውድድሩን ይችሉታል ወይ በሚለው ላይ ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በንግድ ትርኢቱ የተሳተፉ አምራቾችም እንዳሉት ትርኢቱ እራስን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የግብአት አቅራቢ ለማግኘት እንደሚረዳቸው ገልፀዋል፡፡

25ኛው የአዲስ ቻምበር  የንግድ ትርኢት በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማእከል ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *