ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር አገራችንን ክፉኛ እየጎዳት ነው ተባለ::

በትንሹ በአመት ወደ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ይወጣል፤ ይህም ከኤክስፖርት ገቢያችን ጋር ይስተካከላል፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ያስጠናው አንድ ጥናት እንዳመለከተው በሕገወጥ /በኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ ከአገር የሚገባውም ሆነ የሚወጣው የገንዘብ ሃብት በአገሪቱ እድገት ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እያሳረፈ ነው፡፡

ሙስና ፡ ግልፅነት የጎደለው የቀረጥ እና የግብር አሰራር መኖሩ፡ የጥቁር ገበያው መበራከት፡ በአንዳንድ አስመጪዎች እና ላኪዎች የሚፈጸሙት በሃሰተኛ ደረሰኞች ማጭበርበር ለሕገወጡ የገንዘብ እንቅስቃሴ ዋና ዋና ምክንያቶች አንደሆኑ ተመልክቷል፡፡

ለምሳሌ በፈረንጆቹ 2018 ዓም ወደ 3 ቢሊየን የሚሆን የአሜሪካን ዶላር በሕገወጥ መንገድ እንደወጣ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው ሃሰተኛ ዋጋ ደረሰኞችን አንደተወራረደ ተገልጿል፡፡

ከወጪ ንግዳችን ሌላ የምንዛሬ ምንጭ የሆነው በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጰያውያን ወደ አገር ቤት የሚላከው ገንዘብ ነው፡፡

ይህ በውጪ ምንዛሬ መልክ የሚገባው ገንዘብ በጣም ከፍተኟ እንደሆነ እና አንዳንዴም ከአገሪቱ አመታዊ የኤክስፖርት ገቢ ከፍ ያለ ነው፡፡

ነገር ግን እስከ 5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የሚደርሰው ይኸው ገንዘብ እስከ 80 በመቶ የሚሆነው የሚገባው በጥቁር ገበያ አዘዋዋሪዎች በኩል ነው ሲሉ ጥናት አቅራቢው አቶ ይርጋ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

የውጪ ምንዛሬ እጥረት መኖሩ፤ ጠንካራ የገንዘብ ፈሰት ቁጥጥር አለመኖር ከሕጋዊው የምንዛሬ ተመን ይልቅ የጥቁር ገበያ ምንዛሬ ከፍተኛ መሆኑ ለሕገወጥ ዝውውሩ ገፊ ምክንያቶቸ ናቸው ተብሏል፡፡

የብሔራዊ ባንክ እና ሌሎች የሕግ ማስከበር ተቋማትን የቁጥጥር አቅም ማሳደግ፤የቀረጥ አና የግብር ሰብሳቢ መ/ቤቶች አሰራራቸውን ማዘመንእና በቅንጅት መሥራት፤ በባንኮች እና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን የምንዛሬ ተመን በማጥበብ ተወዳዳሪ አንዲሆን መሥራት ከመንግሥት ይጠበቃል የሚሉት ምክረሃሳቦች በጥናቱ ተሰንዝረዋል፡፡

ለጥናቱ ማዳበሪያ ይሆን ዘንድ ከውውይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሃሳቦች እና አሰተያየቶች ተነስተዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል በብሔራዊ ባንክ፤በፋይናንስ ደሕንነት ፤በጉምሩክ እና በገቢ ሰብሳቢ መ/ቤቶች መካካል ዘመናዊ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት እዲዘረጉ እና በቅንጅት አንዲሰሩ ማገዝ ፤ በድንበር አካካባቢ ቁጥጥር ማጠናክር እና ከጎረቤት አገራት ጋር በትብብር መሥራት፤ ለሕብረተሰቡ እና በትህርት በቶች ጭምር ስለሕገወጥ ገንዘብ ዘውውር አስከፊነት ትምህርት መስጠት ፤ ከውጪ የሚላኩ የቤተሰብ ሀዋላዎች ሕጋዊ መስመር እንዲከተሉ የሚያስችሉ አሰራሮች መዘርጋት ያስፈልጋል የሚሉት ይገኙበታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *