አዲስ ቻምበር አመታዊ የሚዲያ ቀኑን ከብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ጋር በመሆን አከበረ፡፡

አዲስ ቻምበር የራሱን የማህበረሰብ ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያን ለማቋቋም እቅድ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት/ አዲስ ቻምበር/ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር በሀገሪቱ ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና እያበረከተ መሆኑን የምክር ቤቱ ዋና ጸኃፊ አቶ ሺበሺ ቤተማርያም  ለታዳሚው ተናግረዋል፡፡

የንግድ ምክር ቤቱ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ከሚዲያ ተቋማት ጋር በመተባበር በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ለተሰማራው ህብረተሰብም ሆነ ወደፊት ለሚመጡ ስራ ፈጣሪዎች ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ በማቅረብ የኢትዮጰያ ኢኮኖሚን መደገፍ ነው ብለዋል።

አቶ ሺበሺ ንግድ ምክር ቤቱ 76ተኛ አመቱን ማስቆጠሩን አውሰተው የቻምበሩን ስራዎች ለማስተዋወቅ  ከመንግስትና የግል ሚዲያዎች ጋር  አብረን መስራታችንን እንቀጥላለን ብለዋል፡

በቻምበር – ሚዲያ ቀን አከባባር ላይ የተገኙት  የፋና ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው በበኩላቸው  ለሁለንተናዊ እድገት በጋራ ስንሰራ አብረን እናድጋለን ያሉ ሲሆን ከአዲስ ቻምበር ጋር የመሰረቱት ግንኙነት የንግድ ምክር ቤቱ ስራዎች  ተደራሽ እንዲሆኑ  በማድረግ ረገድ ተቋማቸው  እንደሚሰራ ገልፀዋል ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ መሪ ቃሉ ‹በሕይወት ፍጥነት › የሚል መሆኑን አስታውሰው መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ፡፡

እክለውም ሁላችንም የተለያዩ ሚዲያዎች  ላይ የምንሰራ ቢሆንም  ሳንገፋፋ አብረን ልንስራ ይገባል ሲሉ  ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በንግድ ምክር ቤቱ የሚዲያ ቀን ላይ  የህትመትና የብሮድካስት ሚዲያ አመራሮች እንዲሁም ጋዜጠኞች  ተገኝተዋል፡፡

በእለቱም አዲስ ቻምበር ለንግዱ ህብረተሰብ መረጃዎቹን በየሳምንቱ በራዲዮ እና በቴቪ ፕሮግራሞቹን እንዲያቀርብ ላስቻለው ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከፍተኛ ምስጋናውን በእድምተኛው ፊት አቅርቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *