‘የአደይ እንቁጣጣሽ 2015 ኤግዚቢሽንና ባዛር’ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል ተከፊተ::

ከ500 በላይ ተሳታፊዎች ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡበት 15ተኛው የአደይ እንቁጣጣሽ የንግድ ትርኢትና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፈተ።

ባዛሩ ለ22 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ500 በላይ ነጋዴዎች የሚሳተፉበት ነው ።

ከግማሽ ሚሊየን በላይ ጎብኝዎች እንደሚሸምቱበት በሚጠበቀዉ ባዛር ላይ ከተለያዩ የዉጪ ሀገራት የተወጣጡ ተሳታፊዎችም ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዉበታል።

የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ታደሰ፤ የዋጋ ንረትን ለመቀነስና ሻጭና ሸማችን በአንድ ለማገናኘት ኤግዚቢሽንና ባዛሮች ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ብለዋል።

የኪራይ ዋጋ በማናርና የጎብኚዎችን የመግቢያ ዋጋ በባዛር ግብይት ላይ እንዲጨምር የሚያደርጉ ሁኔታዎች እየበዙ በመሆኑ ማዕከሉ በራሱ ባዛሮችን እያዘጋጄ መሆኑን ገልፀዋል።

ከከተማ አስተዳደሩና ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት እየተደረገ ያለው ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዘዳንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ፤ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች የተለያዩ ምርቶች በአንድ ቦታ እንዲገኙና የሻጮችና ሸማቾች ጊዜ እንዲቆጠብ አስተዋፅኦ አላቸው ብለዋል።11:57

August 22, 2022

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *